ኢሬቻ ወጣት፣ አዛውንት፣ ህፃን፣ አዋቂ ሳይል በ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ኢሬቻ ወጣት፣ አዛውንት፣ ህፃን፣ አዋቂ ሳይል በሀገራችን ማህበረሰብ ከብረት በጠነከረ አንድነት የሚከበር የአብሮነት መገለጫ በዓል ነው። አቶ በላይ ደጀን

ኢሬቻ ወጣት፣ አዛውንት፣ ህፃን፣ አዋቂ ሳይል በሀገራችን ማህበረሰብ ከብረት በጠነከረ አንድነት የሚከበር የአብሮነት መገለጫ በዓል ነው። አቶ በላይ ደጀን

መስከረም 21 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከሸገር ከተማ ጋር በመቀናጀት ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ምክንያት በማድረግ”ኢሬቻ ለባህላችን ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል የወጣቶች የማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ ።

ለውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ ወጣቶች በጋራ በመሆን የሚደረገው ውይይት በዓሉ የፍቅርና አንድነት ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በዓሉን በባለቤትነት የሚያከብሩበት መሆኑን ከማሳየቱ ባሻገር የወንድማማችንት እና እህትማማችነት ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

ኢሬቻ ወጣት፣ አዛውንት፣ ህፃን፣ አዋቂ ሳይል፣ በሀይማኖት ሳይለያይ፣ በፖለቲካ ሳይነጣጠል በሁሉም የሀገራችን ማህበረሰብ ከብረት በጠነከረ አንድነት ካለምንም ልዩነት የሚከበር የአብሮነት መገለጫ በዓል ነው መሆኑን አቶ በላይ ተናግረዋል።

ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በሰላም እንዲከበር የሁለቱ ከተማ ወጣቶች በቅንጅት እንዲሰሩ የቢሮው ሀላፋፊው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ም/ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ያሸጋገረዉን አምላኩን የሚያመሰግንበትና መጪዉን ዘመን የሰላምና የደስታ እንዲሆንለት የሚለምንበት በዓል መሆኑን ገልጸው በዓሉ ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነት፣ ባህልና እሴቶች የደመቀች መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ኢሬቻ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ቅርሶቻች መካከል አንዱ በመሆኑ በርካታ ቱሪስቶች የሚጎርፍበት የበረከት በዓል ነው ያሉት አቶ አለማየሁ የሁለቱ ከተሞች ትስስር በበዓል ብቻ የሚታጠር ሳይሆን በተጀመሩ የሰላም የልማት እና የብልጽግና ስራዎች ላይ የሁለቱ ከተማ ወጣቶችና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ምልክት በመሆኑ ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ በርካታ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄሰቦች በጋራ እያከበሩት እንደሚገኝ የገለጹት የሸገር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ በበዓሉ ታሪካዊ ዳራ ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገው በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ የሁለቱ ከተማ ወጣቶችን አመስግነዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.