ቢሮው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሶስት ወ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    1

ቢሮው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት የእቅድ አፈፃፀምን ሪፖርትን ገመገመ።

ቢሮው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት የእቅድ አፈፃፀምን ሪፖርትን ገመገመ።

በከተማ ደረጃ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ውስጥ 76 ከመቶ ወጣቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ባለፉት ሦስት በሶስት ወራት ወስጥ ከ21 ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሯል

መስከረም 27 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር ገመገመ።

መድረኩ በማወያየት የተግባር ምዕራፍ የስራ አቅጣጫ ያስቀመጡት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ስፓርቱን ለማስፋፋት የተስሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው ተቋማዊ አስራርን በመዘርጋት በማሕብራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የበጀት ዓመቱን አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ ያደደረጉት የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በስፓርት ፌስቲቫል የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በትምህርትና ሰልጠና፣ በስፓርት ውድድር፣በፌስቲቫል፣በወጣት ስብዕና መገንቢያዎች ስፓርትን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ከመጠቀም አንጻር የተገኙ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል

የፕሮሰስ ካውንስል አባላት በዝግጅት ምዕራፍ በወጣት እና በስፓርት ዘርፍ የተስሩ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልጸው የተግባር ምዕራፍ አፈጻጸምን ከፍ ለማድረግ በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል

አቶ በላይ ደጀን በማጠቃለያ ንግግራቸው በሩብ ዓመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ደካማ ጎኖችን እርምት ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ጠቁመው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ዳይሮክቶሬቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል

ቢሮው በበጀት አመቱ የከተማውን ወጣቶች በከተማዋ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በዝግጅት ምዕራፍ የተሰሩ ስራዎች በተግባር ምዕራፍ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራ አሳውቋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

All reactions:

188Meshu Man, አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 186 others


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.