
በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተመዘገቡ ጠንካራ አፈጻጸሞች ለተግባር ምዕራፍ ስራዎች ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው/አቶ በላይ ደጀን
በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተመዘገቡ ጠንካራ አፈጻጸሞች ለተግባር ምዕራፍ ስራዎች ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው/አቶ በላይ ደጀን/
መስከረም 29 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በ2017 በጀት አመት በዝግጅት ምዕራፍ የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ውስጥ 76 ከመቶ ወጣቶች መሆናቸው እና ከ21 ሺ በላይ ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩ ለተግባር ስራዎቻችን ምቹ መደላድል መሆናቸውን አስታወቁ
ቢሮው የከተማውን ወጣቶች በከተማዋ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩሩት እንደሚሰራ የገለጹት አቶ በላይ የስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ርብርብ እንደሚደረግ ገልጸዋል
ባለፉት ሦስት ወራት በወጣት እና በስፓርት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በየደረጃው ከሚገኙ ኃላፊዎች ጋር መገምገሙን ያስታወሱት ቢሮ ኃላፊው ቅንጅታዊ አሰራርን በመከተል ውጤታማ ለመሆኑ ሁሉም የቢሮ መዋቅሮች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል
የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ስፓርቱን ከማስፋፋት ባለፈ አገር አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ውድድሮች ቀጣይ የትኩሩት አቅጣጫዎች መሆኑን የገለጹት አቶ በላይ በማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ የወጣቶች ግንዛቤ ፈጠራ እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስፋት ላይ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
All reactions:
87Meshu Man, አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 85 others
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.