
በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተከናወኑ ወጣት ተኮር ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ
በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተከናወኑ ወጣት ተኮር ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ
ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ፍላጎት መሰረት በማድረግ የሚሰጣቸ ወጣት ተኮር ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ
የወጣቶች የማብቃት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይሁኔ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹልን የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ወጣቶች በፍላጎታቸው የሚሰሩበት የሚሰጡ አገልግሎቶች በመጠቀም ራሳቸውን ካልባሌ ነገር በመጠበቅ በአገር ፍቅር ስሜት በመታነጽ እሴቶቻቸውን የሚያሳድጉበት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ግንባታ በሁሉም ወረዳዎች በማዳረስ አገልግሎት በማዘመንና ደረጃቸውን በማሻሻል ባለፈው ሩብ ዓመት 1,283,341 ወጣቶች በማዕከላቱ በሚሰጡ አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻሉን የገለጹት አቶ ለ110 የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ማየት ለተሳናቸው ወጣቶች የጃውስ አፕሊኬሽን መጫን መቻሉን ነግረውናል፡፡
የወጣቶች ስብእና መገንቢያ ማእከላት በቴክኖሎጂ ታግዘው ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎት በመስጠት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የነገሩን አቶ ንብረት ለአራት የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት 20 ኮምፒተሮችን ድጋፍ በማድረግ የአገልግሎት አስጣጣቸውን እንዲያሻሻሉ ማድረግ ተችሏል፡፡
የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ዋና ተግዳሮት የሆነውን ጣልቃ ገብነትን ለመፍታት እና ማዕከላቱን ሳቢ እና ማራኪ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
All reactions:
92አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 91 others
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.