
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከታላቁ ሩጫ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የሦስት ዓመት የስራ መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡
ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከታላቁ ሩጫ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የሦስት ዓመት የስራ መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተልዕኮው አድርጎ ከሚሰራባቸው ስራዎች አንዱ የአገራችንን አትሌቲክስ መደገፍ መሆኑ በስምምነቱ ወቅት የተገለጸ ሲሆን ይህንንም ለማጎልበት እና የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሁለቱ ተቋማት ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ ተስማምተዋል፡፡
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኘ እና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ የስምምነት ፊርማውን ሲያካሂዱ የፌደሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የጋራ ስምምነቱም ካካተታቸው ተግባራት ውስጥ በፌደሬሽኑ በኩል የሙያዊ ድጋፍ ማቅረብና አትሌቶች በውድድሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማመቻቸት መሆኑ ተመልክቷል
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ለተተኪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ማመቻቸት፤ ፌደሬሽኑ ለሚያደርጋቸው ውድድሮች ሙያዊና ቁሳዊ እገዛ ማድረግ፤ ፌደሬሽኑ የሚሰራባቸውን የታዳጊ አትሌቶች ፕሮጀክቶች መደገፍ እና የአትሌቲክስ መሰረት ልማት ላይ በጋራ መስራት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ህዳር ቀን የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ በየዓመቱ ከክፍያ ነፃ በሆነ ተሳትፎ ከ500 በላይ አትሌቶችን በውድድሩ ላይ ያሳትፋል፡፡
በታላቁ ሩጫ በ24 ዓመት ቆይታ በውድድር አሽናፊ የሆኑ አትሌቶች በሪሁ አረጋዊ፤ ሰለሞን ባረጋ፤ ሞስነት ገረመው፤ መልክናት ውዱ፤ ትግስት ከተማ፤ ያለምዘርፍ የኋላው፤ አቤ ጋሻው፤ ፎይተን ተስፋይና ቢንያም መሃሪ መሆናቸው ተወስቷል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.