
ወርልድ ቴኳንዶ ፌዶሬሽን የኃይሌ ቤስት ስፓርተኞችን በሜቄዶንያ አስመረቀ
ወርልድ ቴኳንዶ ፌዶሬሽን የኃይሌ ቤስት ስፓርተኞችን በሜቄዶንያ አስመረቀ
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ለ1ሺ አረጋውያን የምሳ ግብዣ ተደርጓል
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ወርልድ ቴኴንዶ ፌዴሬሽን ከኃይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ጋር በመተባበር የ2017 ተማሪዎቹን በሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አስመረቀ
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን አመራሮች፣የስፖርቱ ባለሙያዎች፣ ተመራቂዎች፣የተማሪ ወላጆች፣ አሠልጣኞችና ሲኒየር የማርሻል አርት አስተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ለመቄዶኒያ መስራች ዶክተር ቢኒያም በለጠ እና ለአቶ ጥላሁን ዋሲሁን የክብር ብላክ ቤልት/ጥቁር ቀበቶ ከሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ክለብ
ተበርክቶላቸዋል።
የኃይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ክለብ የሰልጣኞች ምርቃት መርሃ ግብር ላይ የአረጋዊያን ማረፊያ ስፋራ ጉብኝት፣ልዩ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች፥የባህላዊና ዘመናዊ ውዝዋዜ ፕሮግራም ፥ልዩ የሙዚቃ ባንድ ዝግጅት መከናወኑን የገለጹልን የወርል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ዋሲሁን ስፓርተኞች ጤናቸውን ከመጠበቅ ባሻገር በበጎ ፈቃድ ስራዎች የሚሰጡትን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ አገልግሎት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
የኃይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ባለቤት ማስተር ኃይለየሱስ ፍሰሀ በበኩላቸው ከ100 በላይ ስፓርተኞች መመረቃቸውን ገልጸው በዝግጅቱ ላይ ለአንድ ሺ አረጋውያን የምሳ ማብላት ፕሮግራም ከመካሄዱ ባሻገር ንፅህና መጠበቂያ፣ ሶፍት፣ ሳሙና፣ዳይፐር እንዲሁም የአልባሳት ስጦታ መበርከቱን ነግረውናል
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የበጎ አድራጎት ማህበር በቀጣይ በከተማ ደረጃ በሁሉም የስፖርት ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራትየመቄዶኒያ የአረጋዊያን መርጃ መዕከል የሰጡትን ይሁንታ የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ኃላፊነት መውሰዱ ተመልክቷል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.