
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ21ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል። አቶ በላይ ደጀን
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ21ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል። አቶ በላይ ደጀን
ቢሮው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀሙን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ውይይት ከመላው ሰራተኞች ጋር አካሄደ
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ያለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም በመዳሰስ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት በመያየት ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው በተግባር ምዕራፍ ተቋማዊ አስራርን በመዘርጋት በስፓርት እና በወጣት ዘርፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አዲስ አበባ የአገራችን ብሎም የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ ስፖርት ቤተሰቡ እና ወጣቱ የማይተካ ሚና አላቸው ያሉት አቶ በላይ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ እንዲሁም ስፓርቱን ለማስፋፋት በተግባር ምዕራፍ በስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በመጀመሪያው ሩብ አመት በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ21ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ያወሱት አቶ በላይ በተግባር ምዕራፍ የባለድርሻ አካላት እና የቢሮው ሰራተኞች የነበራቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በከተማው እየተሰሩ ያሉ የኮሊደር ልማቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አካተው መሰራታቸው የከተማውን በተለይ የወጣቶችን የዘወትር ጥያቄ የሆነውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ጥያቄ የመለሱ እንዲሁም ለወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን አቶ በላይ ገልፀዋል ።
አቶ ዳዊት ትርፉ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና የስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው በአንደኛው ሩብ አመት ቢሮው ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ገልፀው በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የቢሮውን የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን የቢሮው የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ ያቀረቡ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የከተማውን ወጣቶች በከተማው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ እና የከተማዋን ሁለንተናዊ ስፖርት ልማት እድገት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።
ቢሮው የከተማውን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በማስተባበር በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ችግኝ ተከላ፣ የቤት እድሳት እና የደም ልገሳን ጨምሮ 14 የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በማከናወን ከ1.5 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን በሪፖርቱ ላይ ተጠቁሟል።
ከከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት በመደረጉ እንደሀገር የተከበሩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓሎች እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ መደረጉን ተጠቅሷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.