ንቁ ብርቱ ጀግና ነጻ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ንቁ ብርቱ ጀግና ነጻ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰልጠና በወዳጅነት ፓርክ በድምቀት ተከፈተ

ንቁ ብርቱ ጀግና ነጻ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰልጠና በወዳጅነት ፓርክ በድምቀት ተከፈተ

ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በመተባበር በውፍረት፣ በኮልሰትሮል፣ በስኳር፣ በደም ግፊት እና በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉ የመክፈል አቅም የሌላቸው 1ሺ ሰዎችን የሚያሳትፍ የነጻ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና በወዳጅነት ፓርክ በድምቀት ተጀመረ

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፍ ባሰሙት ንግግር ቢሮው የስፖርት ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ ሰዎች በሚማሩበት፣ በሚሰሩበት፣ በሚኖርሩበት እና በሚዝናኑበት ቦታ ስፖርት እንዲያዘወትሩ በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይሄ የነጻ የአካ ብቃት እንቅስቃሴ የመክፈቻ ዝግጅት የሰልጣኞችን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር ለሌሎች አካትም ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በመሆኑ የሐሳቡ ባለቤት ማስተር ሄኖክ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡

በተለያዩ የጤና እክል ውስጥ ያሉ ወገኖችን በስፖርት ለማከም በይዘቱም በአይነቱም ልዩ ሆኖ የተዘጋጀውን ነጻ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና ማህበረሰቡን ለማንቃት ያለው ፋይዳ በማየት ድጋፍ እያደረግን ነው ያሉት አቶ ዳዊት የዘመናዊ አኗኗር መገለጫ የሆነውን ስፖርትን ባህል በማድረግ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር የውጭ ምንዛሪን ማዳን ይቻላል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ በበኩላቸው አንዲህ አይነት ስልጠናዎች ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ የአመጋገብ ሥርዓታችን በማስተካከል እና ስፖርትን ካዘወተርን ወደምንፈልገው ግብ መድረስ እንደሚያስችል ገልጸው ተላላፊ ያለሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ወቅቱ የፈቀደልንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አካል ብቃት ለአገር ሁለንተናዊ እድገት የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሐሳቡ ባለቤት እና የስልጠናው ዋና ሥራ አስኪያጅ ማስተር ሄኖክ ኪዳነወልድ በውፍረት፣ በኮልሰትሮል፣ በስኳር፣ በደም ግፊት እና በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉ የመክፈል አቅም ሌላቸው ዜጎች ሳይንሳዊ የሆነ ሰልጠናዎች በተለያዩ አማራጮች በመስጠቱ በርካታ ውጤት መመዝገቡን አስታውሰው ማህበሩ የስርዓት ምግብ እና ሕይወት ከህሎት ስልጠና በመስጠት ጤናማ፣ ንቁ፣ ጀግና ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ለሦስት ወራት በሚቆየው የ1ሺ ዜጎች የስፖርት ስልጠና የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች 30,000,000(ሰላሳ ሚሊዮን) የሚገመት አገልግሎት በነፃ ከመሰጠቱ ባሻገር ከሱስ ተስፋ ከመቁረጥ በመመለስ ብርቱ ንቁ ጀግና አምራች ዜጋ በማድርግ በአገር እድገት ላይ አሻራቸወን እንዲያሳርፉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ማስተር ሔኖክ ቅድመ መከላከለልን መሰረት ያደረገ የማሕበረሰብ ጤና ስፖርት እንዲስፋፋና ብዙዎች ካለባቸው የጤና እና የስነ ልቦና ስብራት ለማውጣት በዓመት ለ10ሺ ሰዎች ስልጠና ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.