የስፖርት ማህበራት ማደራጃና ውድድር ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ አያሌው ታደለው

ወጣቶች ከተማ አስተዳደሩ በፈጠራቸው የሥራ ዕድሎች በተለይም በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፎች ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ በበጎፍቃድ ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፉ፣ በየደረጃው ባሉ የወጣት ማህበራት ተሳታፊ በማድረግና ወጣቶች ሁለንተናዊ ስብእናቸው እንዲጎለብት በከተማዋ በተገነቡ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወነ ሲሆን በስፖርት ዘርፍም ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራምን በመተግበር፣ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በየደረጃው በመገንባትና በማስፋፋት፡ የስፖርት ማህበራትን በማደራጀት ኅብረተሰቡን በተለይም ወጣቱን በስልጠናና ውድድር ተጠቃሚ በማድረግ ከፍተኛ ተግባራት ተከናውኗል፡፡ መንግስትም የወጣቶችን እና የስፖርትን ጉዳይ እንደ ዋና የልማት አጀንዳ በመያዝ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ በአገሪቱ ብሎም በከተማችን በተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ወጣቶችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር የተመዘገበው ውጤት እንደተጠበቀ ሆኖ እድገቱ ራሱ የፈጠራቸው አዳዲስ ፍላጎቶችና አስቀድመው በወጉ ያልተቀረፉ ችግሮች ተደማምረው አሁንም የወጣቶችን ዘርፈ ብዙና አንገብጋቢ ችግሮች በሚፈለገው ደረጃ መፍታት አልተቻለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከከተማዋ ዕድገት አኳያ ሲታይ ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማስፋፋት፣ የስፖርት ማዘውተርያ ሥፍራዎችን ተደራሽ ከማድረግ፣ ከታችኛው ዕድሜ እርከን ጀምሮ ዘመናዊ ስልጠናን ከመስጠት፣ የስፖርት ማህበራት በገቢ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ከማድረግ እና ባለሀብቱ በስፖርት መሰረተ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች ባለመመቻቸታቸው በሚፈለገው መልኩ ውጤት ማስመዝገብ አልተቻለም፡፡
በዳይሬክቶሬት ስር ያለው አገልግሎት፡-:
ምንም አልተገኘም.