ክስተቶች

ውስጥ ስፖርት

image description
የመጀመሪያ ቀን icon
የመጨረሻ ቀን icon
አካባቢ አዲስ አበባ

ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ጥር 17 ይጀምራል

ጥር 15 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ጥር 17/2017ዓ.ም መካሄድ ይጀምራል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን ከተማ አቀፍ የፖሊስ ሰራዊት ውድድሩን እና ፌስቲቫል አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች እና የክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ለረጅም አመታት ተቆርጦ የነበረው የፖሊስ ሰራዊት ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል መጀመሩ ለከተማው ብሎም ለሀገር ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተናግረዋል።

ፖሊስና ስፖርት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ ስፖርታዊ ውድድሮችን መዘጋጀታቸው ስፖርቱን ባህሉ ያደረገ፤ ብቁ፣ ጠንካራና ፖሊሳዊ አቋም ያለው ሰራዊት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

የሀገራችንን ስም እና ሰንደቅ አላማ በአለም የስፖርት የውድድር መድረክ ከፍ ያደረጉ በርካታ ስፖርተኞች ከፖሊስ ሰራዊት መውጣታቸውን ያስታወሱት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ በቀጣይ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በስምንት የስፖርት አይነቶች በሁለቱም ፃታ ከጥር 17 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል እንደሚካሄድ የተናገሩት አቶ በላይ 11ዱም ክፍለ ከተሞች እንዲሳተፉ ገልፃዋል።

የውድድሩ ዋና አላማም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚዘጋጀው የፖሊስ ሰራዊት ስፖርታዊ ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በየስፖርት አይነቱ የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ እንደሆነ የቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል።

በአዲስ አበባ ስታድየም ቅዳሜ ጥር 17 በድምቀት በሚጀምረው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ከስፖርታዊ ውድድር በተጨማሪ የተለያዩ ወታደራዊ የሰልፍ ትርኢቶች፣ በፖሊስ የሰለጠኑ የእንስሳት ትርኢቶች እና የተሸከርካሪ ትርኢቶች የሚቀርቡ መሆኑ በውይይቱ የተመላከተ ሲሆን ሁሉም የከተማው ነዋሪ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ እንዲታደም ጥሪ ቀርቧል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+7

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

95You፤ Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 92 ሌሎች

2

11

ይውደዱ

አስተያየት

ያጋሩ

ተጨማሪ አስተያየቶችን ይመልከቱ

 

  • icon 9:30am - 1:00pm
  • አዲስ አበባ

Related Events