ህትመቶች

የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የክበባት ጥምረት ማቋቋሚያ መመሪያ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ወጣቶች ከተለያዩ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ችግሮች ተላቀው በከተማዋና በሀገራዊ ልማት ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማእከላት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመን በመሆኑ፤ ማእከላቱ ወጣቶች ጊዜያቸውን በንባብና ወቅታዊ መረጃዎችን በመቃኘት የስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች.አይ.ቪ.. ኤድስ ምክርና ምርመራ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆንና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማስፋፋት ጤነኛና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ በሚደረገው ጥረት በሚያግዙበት መልክ እንዲቃኙና እንዲመሩ ማድረግ በማስፈለጉ፤ በወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተቋቋሙ ክበባት በጋራ መድረክ እርስ በእርስ ልምድና ተሞክሮዎቻቸውን የሚጋሩበት፤ ተደጋግፈው በመስራት በተደራጀ አኳኋን በስራዎቻቸው ወጣቶችንና ህብረተሰቡን መድረስ የሚችሉበት፤ በአሰራር፤ አደረጃጀትና የድጋፍ ስርዓት የሚጠናከሩበት ጥምረት መፍጠር በማስፈለጉ፤