ህትመቶች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ማህበራት መቋቋሚያና መተዳደሪያ መመሪያ ቁጥር 12/2015

image description

የሀገራችን ስፖርት በተለያዩ ጊዜያት በአደረጃጀትና በአመራር መዋቅሮች ህዝብ በቁጥር የሚያዳግቱ ውስብስብ ችግሮች ያለፈ እና የነበረ መሆኑ ይታወቃል፣ በዚህ መሰርፈት የኤ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት በስፖርቱ ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ለመጀመሪያ ጊዜ በ1990 ዓ.ም የስፖርት ፖሊሲ በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ መንግስታዊና ህዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶች በአደረጃጀታቸው በመዋቅር ተጠናክረው የተሰጣቸውን እየተወጡ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግከፀደቀበት ጀምሮ በቀጥታ ስፖርቱን የሚወክሉ መንግስታዊ መዋቅሮችን ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እንዲሁም ህዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን በከተማ፣ በክ/ከተማ፣ በወረዳ ደረጃ ምክር ቤቶችን፣ ፌዴሬሽኖችን፣ አሶሴሽኖችንና የስፖርት ኮሚቴዎችን በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች በማቋቋምና ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ሆኖም ግን መዋቅሮች በአደረጃጀታቸው የተጠናከሩ ቢሆኑም ህዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶች ከ1995ዓ.ም እስከ 1997ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ መቋቋሚያና መተዳደሪያ መመሪያዎች ወጥቶላቸው ቢደራጁም የተጠበቀውን ውጤትና የከተማውን ህብረተሰብ የስፖርት ፍላጎት አገልግሎት በመስጠት አርክተዋል ማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ከ1997 - 2003ዓ.ም ድረስ ወጣቶችና ስፖርት በቢሮ ደረጃ የተደራጀ ሲሆን በመቀጠልም ከህዳር 2003-ህዳር 2008ዓ.ም ጀምሮ በኮሚሸን ደረጃ ሆኖ ከህዳር 2008 - 2010ዓ/ም ጀምሮ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በሚል መጠሪያ ሲጠቀም ቆይቶ በ2011ዓ/ም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በአዲስ መልክ ተዋቅሯል፡፡ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የነበረው መዋቅራዊ አደረጃጀት የወጣቱንና የስፖርቱን ስራ በአንድ ላይ አጣምሮ ይዞ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር ----/201-- በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ  ደረጃ በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡

  1. ይህንን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ም/ቤት የስፖርት ማህበራትን የማቋቋምና የማደራጀት ስልጣን በተሰጠው መሰረት የከተማዋን ሕዝባዊ ስፖርት አደረጃጀት ከቀደሙት ችግሮች በመነሳት ጥራት ያለው፣ ወጥ የሆነ ተጠያቂነትና ግልፅነት ያለበት እንዲሁም የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር በአሰራርና በአተገባበር ተስማሚ የሆነ የስፖርት ማህበራት መቋቋሚያና መተዳደርያ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡