የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ጎሳዬ አለማየሁ

ከተማችን አዲስ አበባ በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱባት የፌዴራሉ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት የሚገኙባት ናት፡፡ በመሆኑም የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግና ስፖርትን ባህሉ ያደረገ፣ ጤናማ ዜጋ፣ ብቃት ያለው ስፖርተኛና ህብረተሰብን በመፍጠር የከተማዋን የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ እድገት ማፋጠን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ ወጣቶች ከተማ አስተዳደሩ በፈጠራቸው የሥራ ዕድሎች በተለይም በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፎች ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ በበጎፍቃድ ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፉ፣ በየደረጃው ባሉ የወጣት ማህበራት ተሳታፊ በማድረግና ወጣቶች ሁለንተናዊ ስብእናቸው እንዲጎለብት በከተማዋ በተገነቡ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወነ ሲሆን በስፖርት ዘርፍም ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራምን በመተግበር፣ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በየደረጃው በመገንባትና በማስፋፋት፡ የስፖርት ማህበራትን በማደራጀት ኅብረተሰቡን በተለይም ወጣቱን በስልጠናና ውድድር ተጠቃሚ በማድረግ ከፍተኛ ተግባራት ተከናውኗል፡፡ መንግስትም የወጣቶችን እና የስፖርትን ጉዳይ እንደ ዋና የልማት አጀንዳ በመያዝ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዳይሬክቶሬት ስር ያለው አገልግሎት፡-:
ምንም አልተገኘም.